ፍቅርን ጨርሼዉ፡ከመጣሁ በኋላ፡ ትዝታ ረበሸው፡ ምነው የኔን ገላ

Go down

ፍቅርን ጨርሼዉ፡ከመጣሁ በኋላ፡ ትዝታ ረበሸው፡ ምነው የኔን ገላ Empty ፍቅርን ጨርሼዉ፡ከመጣሁ በኋላ፡ ትዝታ ረበሸው፡ ምነው የኔን ገላ

Post  zerai deres on Mon Dec 03, 2012 5:57 pmእንጀራ ኣልፈልግም
ምን ያደርግልኛል
ትዝታዉን ይዤ
ልሂድ ይበቃኛል

የዚያ ማዶ ሰዎች
ዘፈን ኣያምራቸው
ኣጅሬ ትዝታ
ኣልገባም ቤታቸው::

ፍቅርን ጨርሼዉ
ከመጣሁ በኋላ
ትዝታ ረበሸው
ምነው የኔን ገላ

ይሄ ትዝታ የሚሉት፡
ናፍቆት ነው በሽታ ፡
ቀኑስ ይታለፋል
ኣይችሉትም ማታ

ብፈልግ ባልፈልግ
ብወደው ባልወደው
ብወድም ባልወድም
ኣይ ጠፋም ከጎኔ
የትዝታ ደብር ገዳሙ ነኝ እኔ

ከፊቴ እየቆመ
የሰው ስጋ ለብሶ
ኣዉነት ነው ቅዠት
ኣቃተኝ ጨርሶ

ደግ ደጉን ሳጣ
ሃዘኔም መረረ
ሞትን ሞት ቢወስደው
ይሻለኝ ነበረ::
zerai deres

Posts : 192
Join date : 10/09/2012

Back to top Go down

Back to top


 
Permissions in this forum:
You cannot reply to topics in this forum